ቀጥታ፡

አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 27/2017(ኢዜአ)፦አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ ገለጹ። 

ሶስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ማብቃት ማሳደግና ተወዳዳሪነት ሽግግር ማፋጠን በሚል ርእሰ ጉዳይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።


 

በመድረኩ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ኢንስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፖሊሲና እና ስትራተጂ በመቅረጽ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ እየተሰራ ይገኛል።

በተለይም ከአቅም ግንባታ አኳያ በርካታ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል።


 

የኢንዱስትሪዎችን ማነቆ የሆነውን የመስሪያና መሸጫ ቦታዎች ችግር ለመቅረፍ በተደረገው ጥረትም መሻሻል መታየቱ አንስተዋል።

እንዲሁም የፋይናንስ አቅርቦት ችግራቸውንም ለመቅረፍ ከባንኮች ጋር ትስስር በመፍጠር ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በተደረገላቸው ድጋፍም የሚያመርቷቸው ምርቶች ጥራት እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም