ቀጥታ፡

የአምራች ኢንዱስትሪውን ችግሮች በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መፍታት ተችሏል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 27/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስተሪዎች ችግሮቻቸው እንዲፈቱ ያስቻለ ነው ሲሉ የኢንዱስተሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሦስተኛውን የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ትናንት በይፋ ከፍተዋል።

የኤክስፖው አካል የሆነ የፓናል ውይይት "የአምራች ኢንዱስትሪው አለም አቀፍ የኤክስፖርት ገበያ መዳረሻ አማራጮችን ማስፋትና አለም አቀፍ የንግድ ስርዓቶችን መቀላቀል" በሚል መሪ ሃሳብም ተካሒዷል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት መንግስት ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ ይገኛል፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪውን ችግሮች በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መፍታት መቻሉን አንስተው፤ በዚህም የኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት በማሻሻል ከፍተኛ ለውጦች መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡

ንቅናቄው የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም እንዲጨምር ማስቻሉንም አብራርተዋል

የማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያው የኤክስፖርት ምጣኔው እንዲሻሻል እድል የፈጠረ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በዚህም 64 የሚሆኑ በኤክስፖርት ላይ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም