ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ28ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል 

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 27/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል።

አዳማ ከተማ ከመቀሌ 70 እንደርታ ከቀኑ 9 ሰዓት፣ ኢትዮጵያ ቡና ከሀድያ ሆሳዕና ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ። 

የ28ኛ ሳምንት መርሃ ግብር እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል። 

ኢትዮጵያ መድን ሊጉን በ54 ነጥብ እየመራ ነው። ባህር ዳር ከተማ በ43 ነጥብ ይከተላል።

ኢትዮጵያ ቡና በ42 እና መቻል በ39 ነጥብ ሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃን ይዘዋል።

መቀሌ 70 እንደርታ ፣ አዳማ ከተማ፣ ስሑል ሽሬ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከ15ኛ እስከ 18ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ወራጅ ቀጠና ላይ ይገኛሉ።

የሃዋሳ ከተማው ዓሊ ሱሌይማን በ12 ግቦች የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን እየመራ ነው።

የኢትዮጵያ መድኑ መሐመድ አበራ፣ የመቻሉ ሽመልስ በቀለ፣ የኢትዮጵያ ቡናው አንተነህ ተፈራ፣ የፋሲል ከነማው ጌታነህ ከበደ እና  የአርባምንጭ ከተማው አህመድ ሁሴን በተመሳሳይ 10 ጎሎችን በማስቆጠር ይከተላሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም