የኢትዮጵያ እና አርሜኒያን ታሪካዊ ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች ማጠናከር ይገባል - ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ እና አርሜኒያን ታሪካዊ ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች ማጠናከር ይገባል - ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 25/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ እና አርሜኒያን ታሪካዊ ወዳጅነት በተለያዩ መስኮች የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) ገለጹ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የአርሜንያ አምባሳደር ሳሃክ ሳርግሲያንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው ተወያይተዋል።
ውይይቱ ያተኮረው በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ትብብር ዙሪያ ነው።
የኢትዮጵያ እና አርሜንያ ግንኙነት ጥልቅ ታሪካዊ መሠረት ያለው መሆኑን ሚኒስትሩ በውይይቱ ወቅት አንስተዋል።
ይህን ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ወዳጅነት በኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ በቱሪዝም እና በባህል ዘርፎች የበለጠ መጠናከር እንደሚገባው መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።