ቀጥታ፡

ማንችስተር ሲቲ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2017(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ35ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ ዎልቭስን 1 ለ 0 አሸንፏል።


ማምሻውን በኢትሃድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አምበሉ ኬቨን ደ ብሮይን በ35ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቧን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ለግቧ መቆጠር የጀረሚ ዶኩ አስተዋጽኦ ጉልህ ነበር።

ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ በ64 ነጥብ 3ኛ ደረጃን ይዟል። በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ ለያዘው እቅድ የሚያግዘውን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።

ዎልቭስ በ41 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም