ቀጥታ፡

116ኛው የፖሊስ ምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የግማሽ ማራቶን ሩጫ እየተካሔደ ነው

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2017(ኢዜአ)፦ 116ኛው የፖሊስ ምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የግማሽ ማራቶን ሩጫ እየተካሔደ ነው።


 

መነሻና መድረሻውን ሰሚት አደባባይ ባደረገው የግማሽ ማራቶን ሩጫ፤ የኢትዮጵያ፣ የታንዛኒያ፣ የጅቡቲ  እና የኬንያ የፖሊስ አባላት አትሌቶች ተሳትፈዋል፡፡


 

ውድድሩ በዋናነት 116ኛው የፖሊስ ምስረታ መታሰቢያ በዓልን ለማክበር የተዘጋጀ ከመሆኑ ባለፈ በሀገራቱ የፖሊስ አባላት መካከል ያለውን የእርስ በእርስ ግንኙነት የሚያጠናክር ነው ተብሏል።


 

በውድድሩ የኢትዮጵያ ፖሊስ በ21 ኪሎ ሜትር በሁለቱም ፆታዎች ከአንድ አስከ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አሸናፊ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም