ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሃ ግብሮች

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 24/2017 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት የሶስተኛ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ባህር ዳር ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ከቀኑ 9 ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ባህር ዳር ከተማ በ40 ነጥብ 2ኛ ሲሆን ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ32 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል።

ባህር ዳር ከተማ ካሸነፈ ከኢትዮጵያ ቡና የሁለተኝነት ደረጃን በድጋሚ ይረከባል።

የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና መቻልን ያገናኛል።

የአምናው የሊጉ አሸናፊ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ35 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ መቻል በ38 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። 

አምና ሁለቱ ቡድኖች ዋንጫውን ለማንሳት እስከ መጨረሻው ሳምንት ተፎካክረው ንግድ ባንክ አሸናፊ መሆኑ የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ64 ነጥብ አንደኛ መቻል በ63 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

ማሸነፍ ለሁለቱም ቡድኖች የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ያላቸውን ህልም ለማስቀጠል ይረዳቸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም