አዳማ ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነጥብ ተጋርተዋል 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 22/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አዳማ ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል። 

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዳዋ ሆጤሳ በ42ኛውደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን መሪ ማድረግ ችሎ ነበር። 

መሪነቱ የዘለቀው ለሶስት ደቂቃዎች ነው።  በ45ኛው ደቂቃ ነቢል ኑሪ አዳማ ከተማን አቻ አድርጓል። 

ከእረፍት መልስ ግብ ሳይቆጠር ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል።  

ውጤቱን ተከትሎ አዳማ ከተማ በ22 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ12 ነጥብ የመጨረሻውን 18ኛ ደረጃን ይዟል። 

ቀን ላይ በተደረገ የ27ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ስሑል ሽሬ እና ወላይታ ድቻ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም