ዲፕሎማቶች የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 22/2017(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ተቀማጭነታቸውን ያደረጉ የዲፕሎማቲክ ማኀበረሰብ አባላት ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በተገኙበት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዎች አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ እና አምባሳደር ሃደራ አበራ በተገኙበት ጉብኝት አድርገዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዜጎች የሚሰጠውን አገልግሎት ፣ አሰራር ስልቶች በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሲራጅ ረሺድ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በቀጣይም የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል የተሟላ እና ቀልጣፋ ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተገልጿል።

በመንግሥት የሚሰጡ አገልግሎቶች በኤሌክትሮኒክ በመተጋዝ 12 ተቋማት በአንድ ጣሪያ ሥር 40 የተለያዩ አገልግሎቶችን መስጠት መጀመራቸው ይታወቃል።

ይህም ዜጎች ጊዜያቸውን እንዲቆጥቡ እና አገልግሎቶችን በተሻለ ውጤታማ መንገድ እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመረጃው አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም