ስሑል ሽሬ እና ወላይታ ድቻ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ስሑል ሽሬ እና ወላይታ ድቻ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 22/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት የመክፈቻ ጨዋታ ስሑል ሽሬ እና ወላይታ ድቻ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብርሃኑ አዳሙ በ65ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ስሑል ሽሬ መምራት ችሎ ነበር።
ብዙም ሳይቆይ በ69ኛው ደቂቃ ፀጋዬ ብርሃኑ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል ወላይታ ድቻን የአንድ ነጥብ ባለቤት አድርጋለች።
ውጤቱን ተከትሎ ስሑል ሽሬ በ19 ነጥብ 17ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
ወላይታ ድቻ በ38 ነጥብ ደረጃውን ከ6ኛ ወደ 5ኛ ከፍ አድርጓል።
ምሽት 12 ሰዓት ላይ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኙት አዳማ ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ይጫወታሉ።