በዩኒቨርሲቲው 20 ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅም ያለው የባዮ ጋዝ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

ወላይታ ሶዶ፤ሚያዝያ 22/2017(ኢዜአ)፦የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ያስገነባውና 20 ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅም ያለው የባዮ ጋዝ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

የባዮ ጋዝ ማብለያ ፕሮጀክቱ 300 ሜትር ኪዩብ የማብላላት አቅም እንዳለውም ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በፊት በኤሌክትሪክና በማገዶ ሲያከናውን የነበረውን የምግብ ማብሰል ሂደት ሙሉ በሙሉ በባዮጋዝ ሲስተም ለመተካት የሚያስችለው ነው።

ባዮጋዙ ከተመረተ በኋላም ተረፈ ምርቱ የአፈር ማዳበሪያ ለማምረት እንደሚያስችል ተመላክቷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር)፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ ኢንጂነር አክሊሉ አዳኝ እና ሌሎች የክልል አመራሮች፣የአጋር ድርጅቶች ተወካዮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም