ከተማ አስተዳደሩ ለጤና መድህን አገልግሎት ከፍተኛ ድጎማ እያደረገ ይገኛል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ - ኢዜአ አማርኛ
ከተማ አስተዳደሩ ለጤና መድህን አገልግሎት ከፍተኛ ድጎማ እያደረገ ይገኛል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 22/2017(ኢዜአ)፦ በተያዘው በጀት ዓመት ለጤና መድህን አገልግሎት 1 ቢሊየን ብር የሚደርስ ድጎማ መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል።
በጉባዔው ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የጤና መድህን አገልግሎትን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ አገልግሎቱ ለበርካታ ዜጎች እፎይታ እየሰጠ ቢሆንም በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን መፍታት እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
ከንቲባዋ በተያዘው በጀት አመት አስተዳደሩ ለጤና መድህን አገልግሎት 1 ቢሊየን ብር የሚደርስ ድጎማ ማድረጉን ተናግረዋል።
በቀጣይም ከጤና መድህን አገልግሎት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለይቶ ለመፍታት እንደሚሰራ ገልጸዋል።