የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 22/2017(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤው የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል።


 

ምክር ቤቱ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

ምክር ቤቱ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የቀረቡለትን የስራ ሃላፊዎች ሹመት አጽድቋል።

በዚህም መሰረት፦

1/ ወይዘሮ ቆንጂት ደበላ ኦላ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ፣

2/ አቶ አወሌ መሐመድ ኡመር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ፣

3/ ወይዘሮ አይሻ መሐመድ አደም የአዲስ አበባ ከተማ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም

4/ ሕይወት ሳሙኤል ጸጋዬ(ኢ/ር) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ እና ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር በመሆን ተሹመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም