የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 22/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳሉ።
ስሑል ሽሬ ከወላይታ ድቻ ከቀኑ 9 ሰዓት፣ አዳማ ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።
መርሃ ግብሩ ነገም ቀጥሎ ሲውል ኢትዮጵያ ቡና ከድሬዳዋ ከተማ፣ ፋሲል ከነማ ከሀድያ ሆሳዕና እና መቀሌ 70 እንደርታ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የ27ኛ ሳምንት መርሃ ግብር እስከ ሚያዚያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚቆይ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታውቋል።
ኢትዮጵያ መድን ሊጉን በ51 ነጥብ እየመራ ሲሆን ባህር ዳር ከተማ በ40 ነጥብ ይከተላል።
ኢትዮጵያ ቡና በ39 እና መቻል በ38 ነጥብ ሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃን ይዘዋል።
ሃዋሳ ከተማ፣ አዳማ ከተማ፣ ስሑል ሽሬ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከ15ኛ እስከ 18ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ወራጅ ቀጠና ላይ ይገኛሉ።
የሃዋሳ ከተማው ዓሊ ሱሌይማን በ12 ግቦች የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን እየመራ ነው።
የኢትዮጵያ መድኑ መሐመድ አበራ፣ የመቻል ሽመልስ በቀለ እና የአርባምንጭ ከተማው አህመድ ሁሴን በተመሳሳይ 10 ጎሎችን በማስቆጠር ይከተላሉ።