በተጠባቂው ጨዋታ ፒኤስጂ አርሰናልን አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 21/2017 (ኢዜአ)፦በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ፒኤስጂ አርሰናልን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በኤምሬትስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኡስማን ዴምቤሌ በአራተኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቧን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ተቀይረው የገቡት ብራድሊ ባርኮላ እና ጎንካሎ ራሞስ በጨዋታው ማገባደጃ ላይ ያመከኗቸው ግልጽ የግብ እድሎች የፒኤስጂን የአሸናፊነት ውጤት ይበልጥ ሊያሰፉ ይችሉ ነበር።

ማይክል ሜሪኖ ከእረፍት መልስ ያስቆጠረው ጎል በቪዲዮ በታገዘ ዳኝነት(ቫር) ታይቶ ከጨዋታ ውጪ በመሆኑ ተሽሯል።

ፒኤስጂ ከሜዳው ውጪ ወሳኝ ድል አግኝቷል።

የመልስ ጨዋታው በቀጣዩ ሳምንት ረቡዕ ይደረጋል።

ሁለተኛው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ነገ በባርሴሎና እና ኢንተር ሚላን መካከል ይደረጋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም