የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኀበራት ሕብረት ተመሰረተ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኀበራት ሕብረት ተመሰረተ
አዲስ አበባ ፤ ሚያዝያ 21/2017(ኢዜአ)፡- የክልሎችን እና የከተማ አስተዳደሮችን የዳያስፖራ ማኀበራት በመያዝ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኀበራት ሕብረት ለመጀመሪያ ጊዜ መመስረቱን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ ገለጹ።
ዋና ዳይሬክተሩ በሕብረቱ ማቋቋሚያ ስብስባ የመመሥረቻ እና የመተዳደሪያ ደንብ መፅደቁንና የቦርድ አባላት፣ ፕሬዝዳንት፣ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ዋና ፀሐፊ መመረጡን ጠቁመዋል።
ሕብረቱ በዳያስፖራው ቁልፍ ጉዳዮች ላይ እንዲሰራ ተስፋ እንደተጣለበትም አምባሳደር ፍጹም መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።