በድሬደዋ የቀዳማይ ልጅነት ልማት መርሃ ግብርን ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

ድሬደዋ፣ሚያዝያ 21/2017(ኢዜአ)፦በድሬደዋ አስተዳደር የቀዳማይ ልጅነት ልማት መርሃ ግብርን ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የመርሃ ግብሩ ዓላማ በቀጣይ አገር ተረካቢ ትውልድ ለመፍጠር በህጻናት ላይ ከወዲሁ መደላድል ለመፍጠር መሆኑም ታውቋል።

በመድረኩ ዕድሜያቸው በከተማ አስተዳደሩ ከስድስት ዓመት በታች በሆኑ ህፃናት መሠረታዊ ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸውን ያመላከተ የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ውይይት እየተካሄደ ነው።

መርሃግብሩ በአዲስአበባ መተግበር የጀመረ ሲሆን በመቀጠል በድሬደዋ እና በሌሎች ከተሞች በመስፋት ላይ የሚገኝ መሆኑም ተገልጿል።

በውይይቱ ላይ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የጤና፣የማህበራዊ ልማትና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ፣ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ፣ የአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ከበደ ወርቁ፣ እና የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃርና ሌሎች የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም