ምክር ቤቱ በዛሬው እለት ስብሰባው የእንስሳት ጤና እና ደህንነት ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 21/2017(ኢዜአ)፦የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 27ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ያካሂዳል።

በዚህም የእንስሳት ጤና እና ደህንነት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ ሪፖርት እና የውሳኔ ሀሳብ የሚያቀርብ ሲሆን ውይይት ከተደረገበት በኋላ እንደሚፀድቅ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የተጓደሉ የቋሚ ኮሚቴ አመራሮችን ለመሰየም የሚቀርብ የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም