አቶ አደም ፋራህ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ በነበሩት አቶ አሊ ከድር ድንገተኛ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
አቶ አደም ፋራህ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ በነበሩት አቶ አሊ ከድር ድንገተኛ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2017(ኢዜአ)፦ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ በነበሩት አቶ አሊ ከድር ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ።
አቶ አደም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ መልዕክት አቶ አሊ ዛሬ በጽህፈት ቤቱ ከተካሄደው የአመራሮች ስብስባ ወደ ስራ ሲመለሱ በደረሰባቸው ድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወታቸው በማለፉ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል።
ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ልባዊ መጽናናትን ተመኝተዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ አሊ ከድር ከዚህ ሃላፊነታቸው በፊት የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆንም አገልግለዋል።