በ "ኑ ጎንደርን እንሞሽር" የገቢ ማሠባሠቢያ መርሐ ግብር ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ቃል ተገባ - ኢዜአ አማርኛ
በ "ኑ ጎንደርን እንሞሽር" የገቢ ማሠባሠቢያ መርሐ ግብር ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ቃል ተገባ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 20/2017(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል በተካሄደው የ"ኑ ጎንደርን እንሞሽር" የገቢ ማሠባሠቢያ መርሐ ግብር ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ቃል ተገብቷል።
በመርሃ ግብሩ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ፣ የፌዴራልና የክልሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በዚህም፦
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር የጎንደር አየር ማረፊያን ሙሉ ግንባታ ለማከናወን ቃል ገብቷል።
የሶማሌ ክልል 15 ሚሊዮን ብር፣
የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ 50 ሚሊዮን ብር፣
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ 35 ሚሊዮን ብር፣
የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ማኅበር 100 ሚሊየን ብር፣
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 121 ሚሊየን ብር፣
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት 15 ሚሊየን ብር፣
የአማራ ክልል መንግሥት ለጎንደር፣ ለባሕር ዳር እና ለደሴ ከተሞች የኮሪደር ልማት ሥራዎች ለእያንዳንዳቸው 100 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ቃል የገቡ ሲሆን የመንግስትና የግል የልማት ድርጅቶችም በጎንደር ከተማ ለሚከናወኑ የልማት ስራዎች የሚውል የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።
በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል በተካሄደው የ"ኑ ጎንደርን እንሞሽር" የገቢ ማሠባሠቢያ መርሐ ግብር ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ቃል ተገብቷል።