ናፖሊ የሊጉን መሪነት ከኢንተር ሚላን ተረከበ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 19/2017 (ኢዜአ)፦
በጣልያን ሴሪአ የ34ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ሰባት ጨዋታዎች ተደርገዋል።

የዋንጫ ተፎካካሪዎቹ ኢንተር ሚላን እና ናፓሊ ጨዋታቸውን አካሂደዋል።

በሳንሲሮ ስታዲየም ኢንተር ሚላን ሮማን አስተናግዶ 1 ለ 0 ተሸንፏል።

አርጀንቲናዊው ማቲያስ ሱሌ የማሸነፊያ ግቧን አስቆጥሯል።

በዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ስታዲየም በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ ናፖሊ ቶሪኖን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ስኮት ማክቶሚናይ ሁለቱንም ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቶቹን ተከትሎ ናፖሊ በ74 ነጥብ የሊጉን መሪነት ከኢንተር ሚላን ተረክቧል።

ኢንተር ሚላን በ71 ነጥብ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ዝቅ ብሏል።

የአራት ሳምንት መርሃ ግብር የቀረው የጣልያን ሴሪአ ዋንጫውን ማን ያነሳል? የሚለው ጉዳይ ይበልጥ አጓጊ ሆኗል።

በሌሎች ጨዋታዎች ጁቬንቱስ ሞንዛን፣ ኤሲ ሚላን ቬኔዚያን በተመሳሳይ 2 ለ 0 አሸንፈዋል።

ፊዮረንቲና ኢምፖሊን 2 ለ 1 እንዲሁም ኮሞ ጄኖዋን 1 ለ 0 ሲያሸንፉ አትላንታ ከሊቼ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም