ሊቨርፑል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለ20ኛ ጊዜ ማንሳቱን አረጋገጠ - ኢዜአ አማርኛ
ሊቨርፑል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለ20ኛ ጊዜ ማንሳቱን አረጋገጠ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 19/2017(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ34ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሊቨርፑል ቶተንሃም ሆትስፐርስን 5 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።
ማምሻውን በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሉዊስ ዲያዝ፣ መሐመድ ሳላህ፣ ኮዲ ጋፕኮ፣ አሌክሲስ ማካሊስተር እና የቶተንሃሙ ዴስትኒ ኡዶጊ በራሱ ግብ ላይ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
ዶምኒክ ሶላንኪ ለስፐርስ ብቸኛዋን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ውጤቱን ተከትሎ ሊቨርፑል በ82 ነጥብ አራት ጨዋታ እየቀረ የሊጉን ዋንጫ ለ20ኛ ጊዜ ማንሳቱን አረጋግጧል።
ይህም ሊቨርፑልን የሊጉን ዋንጫ በርካታ ጊዜ የማንሳት ክብረ ወሰንን ከታሪካዊ ባላንጣው ማንችስተር ዩናይትድ ጋር እንዲጋራ አድርጎታል።
ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ37 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል።
በሌላኛው የ34ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ቦርንማውዝ እና ማንችስተር ዩናይትድ አንድ አቻ ተለያይተዋል።