ማንችስተር ሲቲ ለኤፍኤ ካፕ ፍጻሜ አለፈ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 19/2017 (ኢዜአ)፡- በእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ ሁለተኛ የግማሽ ፍጻሜ መርሃ ግብር  ማንችስተር ሲቲ ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ 0 አሸንፏል።

ማምሻውን በዌምብሌይ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሪኮ ሉዊስ እና ጆሽኮ ግቫርዲዮል ለሰማያዊዎቹ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ ለፍጻሜው አልፏል። በፍጻሜው ከክሪስታል ፓላስ ይገናኛል።

ክሪስታል ፓላስ ትናንት አስቶንቪላን 3 ለ 0 ማሸነፉ ይታወቃል።

ሁለቱ ክለቦች የፍጻሜ ጨዋታቸውን ግንቦት 9 2017 ዓ.ም በዌምብሌይ ስታዲየም ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም