በኢትዮጵያ ዋንጫ ሲዳማ ቡና ለፍፃሜ ደረሰ  

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2017(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ሲዳማ ቡና መቻልን በመለያ ምት 7ለ6 በማሸነፍ ለፍፃሜ አልፏል።

ሁለቱ ክለቦች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 0ለ0 በማጠናቀቃቸው ነው ወደ መለያ ምት ያመሩት።

በፍፃሜው ሲዳማ ቡና ከወላይታ ድቻ ጋር የሚገናኙ ሲሆን የፍፃሜ ጨዋታው ግንቦት 30/2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የውድድሩ አሸናፊ ኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ እንደሚሆንም ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም