በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ዩናይትድ እና በርማውዝ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2017(ኢዜአ)34 ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ከበርንማውዝ ጋር ያደረገውን ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት አጠናቋል፡፡

የበርንማውዝን ግብ ሴሜኒዮ በመጀመሪያው አጋማሽ ሲያስቆጥር፤ ሆይሉንድ ማንቼስተር ዩናይትድን አቻ ያደረገች ግብ በጨዋታው መጠናቀቂያ አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ በርንማውዝ 50 ነጥብ 10 ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ ማንችስተር ዩናይትድ 39 ነጥብ 14 ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ተጠባቂው የሊቨርፑል እና ቶተንሀም ሆትስፐር ጨዋታ በአንፊልድ ምሽት 12 ሰዓት 30 ይደረጋል፡፡

ከጨዋታው አስቀድሞ የሊቨርፑል ደጋፊዎች በአንፊልድ አካባቢ ደማቅ የድጋፍ እንቅስቃሴ እያሳዩ ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም