በሴቶች የለንደን ማራቶን ውድድር አትሌት ትዕግስት አሰፋ አሸነፈች

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2017(ኢዜአ) በተጠባቂው የሴቶች ለንደን ማራቶን ውድድር አትሌት ትዕግስት አሰፋ አሸንፋለች።

45ኛውን የለንደን ማራቶን የሴቶች ምድብ ውድድር የፓሪስ ኦሎምፒክ የብር ሜዳልያ ባለቤቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበላይነት ማሸነፏን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል።


 

አትሌት ትዕግስት አሰፋ ውድድሩን 2:15.50 በመግባት በአንደኝነት ስታሸንፍ ኬንያዊቷ አትሌት ጆይስሊን ጄፕኮስጊ ሁለተኛ እንዲሁም ኔዘርላንዳዊቷ አትሌት ሲፈን ሀሰን ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም