የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት የስራ ሀላፊዎች ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት የስራ ሀላፊዎች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2017(ኢዜአ)፦ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ከዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት የስራ ሀላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ በዋሽንግተን ዲሲ እየተካሄደ ካለው እኤአ የ2025 የዓለም ገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ የጸደይ ወቅት ስብሰባ ጎን ለጎን ነው።
አቶ አህመድ ሽዴ የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት ምክትል ጸሀፊ ኤሪክ ሜየር ጋር በሁለትዮሽና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸው ተገጿል።
የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት ምክትል ጸሀፊ ኤሪክ ሜየር የኢትዮጵያ መንግስት እየተገበረ ባለው ሪፎርም ዓለም አቀፍ ችግሮችን መቋቋም የሚችል ኢኮኖሚ እየገነባ በመሆኑ አድንቀዋል።
ኢትዮጵያ እየተገበረችው ያለው የኢኮኖሚ ሪፎርም ኢኮኖሚውን ማዘመንና አብዛሃነት መደገፍ በሚያስችል መልኩ እንዲቀጥል የሚደረገውንም ጥረት እንዲሁ።
አቶ አህመድ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና ቀጣናዊ መረጋጋት እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች የጋራ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላትን የላቀ አጋርነት ለማጠናከር ቁርጠኛ ነች።