ሞገስ ጥዑማይ እና ገመኔ ማሚቴ የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር አሸናፊ ሆኑ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 19/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድርን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ክለብ ሞገስ ጥዑማይ በወንዶች እንዲሁም የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማዋ ገመኔ ማሚቴ በሴቶች አሸናፊ ሆነዋል።

መነሻና መድረሻውን በመስቀል አደባባይ ያደረገው 4ኛ ዓመት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የ2017 ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ተካሂዷል።

በዝግጅቱ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን(ዶ/ር)፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይን ጨምሮ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በውድድሩም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ክለብ ሞገስ ጥዑማይ በወንዶች እንዲሁም የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማዋ ገመኔ ማሚቴ በሴቶች የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር አሸነፊ ሆነዋል።

👉በዚህም በ10 ኪሎ ሜትር የኢትዮጵያ ታምርት የወንዶች የሩጫ ውድድር፦

1ኛ. ሞገስ ጥዑማይ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ የወርቅ ሜዳሊያ እና የ300 ሺህ ብር፣

2ኛ.ጅራታ ሌሊሳ በግል የብር ሜዳሊያና የ200 ሺህ ብር እንዲሁም

3ኛ. ሲዳ አማና ከሸገር ከተማ የነሀስ ሜዳሊያ እና የ100 ሺህ ብር ሽልማት አሸናፊ በመሆን ከኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እና ከኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ እጅ የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ተረክበዋል።


 

👉በተመሳሳይ በ10 ኪሎ ሜትር የኢትዮጵያ ታምርት የሴቶች የሩጫ ውድድር፦

1ኛ. ገመኔ ማሚቴ ከኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ የወርቅ ሜዳሊያ እና የ300 ሺህ ብር፤

2ኛ.አበዙ ከበደ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብር ሜዳሊያና የ200 ሺህ ብር እንዲሁም፤

3ኛ. ማርታ አለማየሁ በግል የነሀስ ሜዳሊያ እና የ100 ሺህ ብር አሸናፊ በመሆን ከባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ እና ከአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ ዕጅ የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ተረክበዋል።

የሩጫ ውድድሩን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን ውድድሩም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ 4ኛ ዓመት ዝግጅትን አስመልክቶ የተሰናዳ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም