የሊጉ መሪ ሊቨርፑል የዋንጫ ባለቤትነቱን ያረጋግጥ ይሆን? - ኢዜአ አማርኛ
የሊጉ መሪ ሊቨርፑል የዋንጫ ባለቤትነቱን ያረጋግጥ ይሆን?

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 19/2017(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ34ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ሊቨርፑል ከቶተንሃም ሆትስፐርስ ጋር ይጫወታል።
ጨዋታው ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ላይ በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም ይደረጋል።
ሊቨርፑል በ79 ነጥብ የሊጉ አናት ላይ ተቀምጧል። ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ37 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል።
ቀያዮቹ በጨዋታው ካሸነፉ ወይም አቻ ከወጡ የሊጉን ዋንጫ ለ20ኛ ጊዜ ማንሳታቸውን ያረጋግጣሉ።
ይህም ሊቨርፑልን የሊጉን ዋንጫ በርካታ ጊዜ የማንሳት ክብረ ወሰንን ከታሪካዊ ባላንጣው ማንችስተር ዩናይትድ ጋር እንዲጋራ ያደርገዋል።
በሌላኛው የ34ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ቦርንማውዝ ከማንችስተር ዩናይትድ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።