በኢትዮጵያ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ሲዳማ ቡና ከመቻል ይጫወታሉ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ሲዳማ ቡና ከመቻል ይጫወታሉ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 19/2017(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ መርሃ ግብር ሲዳማ ቡና ከመቻል ዛሬ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ላይ በሃዋሳ ከተማ ይደረጋል።
በሩብ ፍጻሜው ሲዳማ ቡና ሀድያ ሆሳዕናን፣ መቻል ኢትዮጵያ መድንን በመርታት ለዛሬው ጨዋታ ደርሰዋል።
የሁለቱ ቡድኖች አሸናፊ ከወላይታ ድቻ ጋር ለፍጻሜው ይገናኛል።
ወላይታ ድቻ ትናንት ሸገር ከተማን 2 ለ 0 በማሸነፍ ለፍጻሜ ማለፉ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ክለብ ኢትዮጵያን ወክሎ በቀጣዩ ዓመት በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።