ኖቲንግሃም ፎረስት እና ማንችስተር ሲቲ በኤፍኤ ካፕ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 19/2017(ኢዜአ)፡- በእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ ሁለተኛ የግማሽ ፍጻሜ መርሃ ግብር ኖቲንግሃም ፎረስት ከማንችስተር ሲቲ ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከምሽቱ 12 ሰዓት ከ30 ላይ በዌምብሌይ ስታዲየም ይካሄዳል።

ኖቲንግሃም ፎረስት በሩብ ፍጻሜው ብራይተንን እንዲሁም ማንችስተር ሲቲ ቦርንማውዝን አሸንፈዋል።

በኤፍኤ ካፕ ተሳትፏቸው ታሪክ ኖቲንግሃም ፎረስት ሁለት ጊዜ ዋንጫውን ሲያነሳ ማንችስተር ሲቲ ሰባት ጊዜ በማንሳት ብልጫውን ይወስዳል።

በተጨማሪም ማንችስተር ሲቲ በውድድሩ 6 ጊዜ እና ኖቲንግሃም ፎረስት 1 ጊዜ ለፍጻሜ ደርሰው ሽንፈት አስተናግደዋል።

የሁለቱ ክለቦች አሸናፊ ከክሪስታል ፓላስ  ጋር በፍጻሜው ይጫወታል።

ክሪስታል ፓላስ አስቶንቪላን ትናንት 3 ለ 0 በማሸነፍ ለፍጻሜው አልፏል።

የ40 ዓመቱ ማይክል ኦሊቨር የሁለቱን ክለቦች ተጠባቂ ጨዋታ በዋና ዳኝነት ይመሩታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም