ባርሴሎና የኮፓ ዴል ሬይ ዋንጫን ለ32ኛ ጊዜ አነሳ - ኢዜአ አማርኛ
ባርሴሎና የኮፓ ዴል ሬይ ዋንጫን ለ32ኛ ጊዜ አነሳ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 18/2017(ኢዜአ)፦ በስፔን የኮፓ ዴል ሬይ የፍጻሜ ጨዋታ ባርሴሎና ሪያል ማድሪድን 3 ለ 2 አሸንፏል።
ማምሻውን በዴላ ካርቱጃ ስታዲየም በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ፔድሪ፣ ፌራን እና ኩንዴ ለባርሴሎና ግቦቹን ሲስቆጥሩ ለማድሪድ ደግሞ ኪሊያን ምባፔ እና ኦሪየል ችዌሜኒ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ጨዋታው በመደበኛው 90 ደቂቃ ሁለት አቻ በመጠናቀቁ ቡድኖቹ ወደ ጭማሪ ሰዓት አምርተዋል።
ጁለስ ኩንዴ በ116ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ባርሴሎናን አሸናፊ አድርጓል።
አንቶኒ ሩዲገር በ123ኛው ደቂቃ ቀይ ካርድ ተመልክቷል።
ውጤቱን ተከትሎ ባርሴሎና የስፔን ጥሎ ማለፍ ዋንጫ ባለቤት ሆኗል።
የውድድሩ የበርካታ ጊዜ ባለክብር ዋንጫውን ለ32ኛ ጊዜ ከፍ አድርጓል።