ኢትዮጵያ እና ግሪክ በህጋዊ የስራ ስምሪት በትብብር መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውይይት አካሄዱ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ግሪክ በህጋዊ የስራ ስምሪት በትብብር መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውይይት አካሄዱ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 18/2017 (ኢዜአ)፡- የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ከግሪክ ልዑካን ቡድን ጋር በጽህፈት ቤታቸው ጋር ተወያይተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች፣ በኢትዮጵያ የግሪክ ኤምባሲ እና የግሪክ የፓርላማ ተወካዮች በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል።
ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት ህጋዊ እና የሰለጠነ የሰው ኃይል ስምሪት ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።
ግሪክ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የሚሰማራ የሰለጠነ የሰው ኃይል አቅርቦት ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራት እንደምትፈልግ መግለጿን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።