ወላይታ ድቻ በኢትዮጵያ ዋንጫ ለፍጻሜ አለፈ - ኢዜአ አማርኛ
ወላይታ ድቻ በኢትዮጵያ ዋንጫ ለፍጻሜ አለፈ
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 18/2017 (ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ ዋንጫ የመጀመሪያ የግማሽ ፍጻሜ መርሃ ግብር ወላይታ ድቻ ሸገር ከተማን 2 ለ 0 አሸንፏል።
በሃዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ በተካሄደው ጨዋታ ዘላለም አባተ እና ብዙአየሁ ሰይፈ የማሸነፊያ ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ድቻ ለፍጻሜው ያለፈ የመጀመሪያ ቡድን ሆኗል። ቡድኑ አምና የውድድሩ የፍጻሜ ተፋላሚ ነበር።
ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያደገው ሸገር ከተማ የውድድር ጉዞው ግማሽ ፍጻሜ ላይ ተገቷል።
ወላይታ ድቻ በፍጻሜው ከሲዳማ ቡና እና መቻል አሸናፊ ጋር ይጫወታል።
ሲዳማ ቡና ከመቻል ነገ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ክለብ ኢትዮጵያ ወክሎ በቀጣዩ ዓመት በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።