ሪፎርሙ ገለልተኛ እና ዘመኑን የዋጀ የፀጥታ ተቋም ከመገንባት አንፃር አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው- አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 18/2017 (ኢዜአ)፦ሪፎርሙ ገለልተኛ እና ዘመኑን የዋጀ የፀጥታ ተቋም ከመገንባት አንፃር አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ዛሬ በሐረሪ ክልል የሚገኙ የጸጥታ ተቋማት 116ኛው የኢትዮጵያ ፖሊስ የምስረታ በዓልን አስመልክቶ በከተማው የጽዳት ዘመቻ እና አረንጓዴ ስፍራዎችን እንክብካቤ ማካሄዳቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

የሪፎርሙ አንዱ አካል  የሆነው የተቋም ግንባታ ስራ ብቁ፣ ገለልተኛ እና ዘመኑን የዋጀ የፀጥታ ተቋም ከመገንባት አንፃር አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው ብለዋል።

በተለይም የክልሉ ፖሊስ ከነበሩበት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተላቆ የፀጥታ እና የህግ ማስከበር ስራዎችን በብቃት ከመፈፀም ባለፈ በዚህ አይነት የልማት ስራዎች መሳየተፉ የሰራዊቱን ህዝባዊነት የሚያመላክት እንደሆነም አመልክተዋል።

በቀጣይም የተቋም ግንባታ ስራ ለማጠናከር አስፈላጊውን እገዛ እንደሚደረግ ገልጸው ዛሬ በተካሄደው የልማት ስራ ለተሳተፉ የፀጥታ አመራሮችና አባላት ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም