ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች 

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 18/2017 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ መርሃ ግብር ዛሬ እና ነገ በሃዋሳ ከተማ ይካሄዳል። 


ሸገር ከተማ ከወላይታ ድቻ ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ላይ በሃዋሳ ሰው ሰራሽ ሜዳ ይጫወታሉ።


በሩብ ፍጻሜው ሸገር ከተማ ባህር ዳር ከተማን እንዲሁም ወላይታ ድቻ ሃዋሳ ከተማን አሸንፈዋል። 


ሸገር ከተማ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን ማረጋገጡ ይታወቃል። ቡድኑ በጥሩ ግስጋሴ ይገኛል።

ወላይታ ድቻ አምና የውድድሩ የፍጻሜ ተፈላሚ ነበር። 

ነገ ሲዳማ ቡና ከመቻል ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። 

የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ክለብ ኢትዮጵያ ወክሎ በቀጣዩ ዓመት በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።

የኢትዮጵያ ዋንጫ በ1937 ዓ.ም የተጀመረ አንጋፋ የጥሎ ማለፍ ውድድር ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም