ኢትዮጵያ በብሪክስ ዋና አስተባባሪዎች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በብሪክስ ዋና አስተባባሪዎች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ እየተካሄደ ባለው ሁለተኛው የብሪክስ ዋና አስተባባሪዎች(ሼርፓ) እና ምክትል አስተባባሪዎች(ሶስ ሼርፓ) ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ልዩ ፖሊሲ አማካሪ እና የኢትዮጵያ የብሪክስ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የቴክኒክ ኮሚቴ ሊቀ-መንበር አምባሳደር ምንሊክ ዓለሙ የተመራ ልዑክ በስብሰባው ላይ ተሳታፊ ሆኗል።
ስብሰባው የተመራው በብራዚል ዋና አስተባባሪ(ሼርፓ) እና የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ እና ፋይናንስ ጉዳዮች ፀሐፊ ማውሪሲዮ ካርቫሎ ሊሮዮ ነው።
ሼርፓዎቹ ሚያዚያ 20 እና 21 ቀን 2017 ዓ.ም በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ በሚካሄደው የመጀመሪያው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ የሚቀርብ የጋራ መግለጫ እንደሚያዘጋጁ ተገልጿል።
ስብሰባው የብሪክስ መሪዎች የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ አየር ንብረት ለውጥ ድንጋጌ ዝግጅት እና በዓመታዊ የስራ እቅድ ውስጥ የተያዙ አጀንዳዎችን እንደሚገመግም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።