ኢትዮጵያ በአውሶም የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በአውሶም የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 16/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በዩጋንዳ ካምፓላ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ(አውሶም) የሚኒስትሮች ስብሰባን እየተሳተፈች ነው።
በስብሰባው የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ(ኢ/ር)፣ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እና በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ እንዲሁም ሌሎች ልዑካን ተሳታፊ መሆናቸውን በካምፓላ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።