ቀጥታ፡

የልዑካን ቡድኑ የኢትዮጵያ እና ብራዚል የግብርና ትብብር ማጠናከር ያለመ ጉብኝት እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 15/2017(ኢዜአ)፦ በግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር) የተመራው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በብራዚል የስራ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል።

የልዑካን ቡድኑ ከግብርና ሚኒስቴር እና ከሚኒስቴሩ ተጠሪ ተቋማት፣ ከዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢንስቲትዩት እና የዓለም ባንክ የተውጣጣ ነው።


 

ልዑኩ ከብራዚል ንግድ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምክትል ፀሐፊ ማርሴል ሞሪራ ጋር ተወያይቷል።

የጉብኝቱ አላማ በግብርና ኤክስቴንሽንና ምርምር ላይ ልምድ ለመቅሰምና የሁለትዮሽ ትብብርን ማጠናከር መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም