ቀጥታ፡

በ10 ከተሞች የኃይል ስርጭት መስመሮች መልሶ ግንባታና አቅም የማሳደግ ስራ እየተከናወነ ነው  

አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 15/2017 (ኢዜአ)፦በ10 ከተሞች የኃይል ስርጭት መስመሮች ላይ መልሶ ግንባታና አቅም የማሳደግ ስራ ማከናወን የሚያስችል ፕሮጀክት ወደ ስራ መግባቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ። 

ፕሮጀክቱ በኃይል ስርጭት መስመሮች እርጅና ምክንያት በከተሞች እያጋጠመ ያለውን የኃይል መቆራረጥ ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል እንደሆነም ገልጿል። 

በዚህም በተመረጡ 10 ከተሞች የመልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ስራ ለመስራት ፕሮጀክት ተቀርጾ ወደ ስራ ገብቷል፡፡

የመልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ የሚደረገው በነቀምት፣ አምቦ፣ ሱሉልታ፣ ቢሾፍቱ፣ አሰላ፣ ደብረ ብርሃን፣ ዲላ፣ ሆሳዕና፣ አሶሳ እና ጅግጅጋ ከተሞች መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል። 

ፕሮጀክቱ በሶስት ምዕራፍ ተከፍሎ እንደሚከናወን የአገልግሎቱ መረጃ ያመለክታል ።

በመጀመሪያው ዙር ቢሾፍቱ፣ ሱሉልታ እና ደብረብርሃን፣ በሁለተኛው ዙር አሰላ፣ ሆሳዕና፣ ዲላ እና ጂግጅጋ እንዲሁም በሶስተኛው ዙር አምቦ፣ ነቀምት እና ኦሶሳ ከተሞችን እንደሚሸፍን ተመላክቷል።
 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም