ምክር ቤቱ በዛሬ ውሎው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ በዛሬ ውሎው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 15/2017 (ኢዜአ):- የሐረሪ ክልል የመስተዳድር ምክር ቤት የ2017 የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ዛሬም እንደቀጠለ ነው።
የክልሉ የማህበራዊ ልማት ዘርፍ ተቋማት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ያከናወኗቸውን አበይት ተግባራት የተመለከተ ሪፖርት በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
ምክር ቤቱ በሰው ኃይል እና የመልካም አስተዳደር ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን የተመለከተ ሪፖርትም ያዳምጣል።
ሪፖርቶቹን ተከትሎ ምክር ቤቱ በተነሱ ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚያደርግ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።