በካሜሮን የግዛት አስተዳደር ሚኒስትር የተመራ ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኘ - ኢዜአ አማርኛ
በካሜሮን የግዛት አስተዳደር ሚኒስትር የተመራ ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኘ
አዲስ አበባ ፤ ሚያዝያ 14/2017 (ኢዜአ)፡- በካሜሮን የግዛት አስተዳደር ሚኒስትርና የካሜሮን የሀጅ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ፖል አታንጋ ንጂ የተመራ ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ አየር መንገድን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝቷል።
ልዑካን ቡድኑ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እና የማኔጅመንት አባላት ጋር ውይይት አደርጓል።
በውይይቱ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለካሜሮን የሀጅ ተጓዦች እንዲሁም ወደ ያውንዴ እና ዱዋላ የሚያደርገውን መደበኛ የበረራ አገልግሎት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጡን በመረጃው አመልክቷል።