የኢትዮጵያ ድርጅቶች በዚምባቡዌ ዓለም አቀፍ የንግድ ኤግዚቢሽን እየተሳተፉ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ድርጅቶች በዚምባቡዌ ዓለም አቀፍ የንግድ ኤግዚቢሽን እየተሳተፉ ነው
አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 14/2017 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ ድርጅቶች በዚምባቡዌ ቡልዋዮ ከተማ እየተካሄደ ባለው 65ኛው ዓለም አቀፍ የንግድ ኤግዚቢሽን ላይ እየተሳተፉ ይገኛል።
በኤግዚቢሽኑ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ እና የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ድርጅቶች ተሳታፊ ሆነዋል።
ድርጅቶቹ ከሁነቱ ጎን ለጎን በሚካሄዱ የምክክር እና ልውውጥ ፕሮግራሞች ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
በሀራሬ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የኢትዮጵያ አምራቾች በኤግዚቢሽኑ ላይ የንግድ ትስስር እንዲፈጥሩ እና የተሞክሮ ልውውጥ እንዲያካሂዱ ድጋፍ ማድረጉን በመረጃው አመልክቷል።
ትናንት የተጀመረው ዓለም አቀፍ የንግድ ኤግዚቢሽን እስከ ሚያዚያ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።