ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 14/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቱ ለኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብጽዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ እየሱስ በላኩት የሀዘን መግለጫ በሮማው ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን በመግለፅ ለቤተሰቦቻቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን መመኘታቸውን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም