የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 10/2017(ኢዜአ)፦ የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።
በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተከበረ በሚገኘው የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፣ ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ አባቶች እና ምዕምናን ተገኝተዋል።
በዓሉ በስግደት፣ በፆምና በጸሎት እየተከበረ ይገኛል።