ቀጥታ፡

ኢዜአ የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቋሚነት ለሚያግዛቸው የተማሪ ቤተሰቦች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 9/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቋሚነት ለሚያግዛቸው የተማሪ ቤተሰቦች በዓሉን የሚያሳልፉበት ድጋፍ አድርጓል።


 

በኢዜአ የሴቶችና ባለብዙ ዘርፍ ዳይሬክተር ወይዘሮ ታደለች ቦጋለ እንደገለጹት ተቋሙ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ተማሪዎች ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በቋሚነት ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።

በዛሬው እለትም 17 ተማሪዎች የትንሳኤ በዓልን ከወላጆቻቸው ጋር በደስታ እንዲያከብሩ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል።

የተደረገው ድጋፍ የተቋሙ ሰራተኞች በየወሩ ከደመወዛቸው በፍቃደኝነት በሚያደርጉት መዋጮ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከአስተማማኝ ዜና ምንጭነቱ ባሻገር ማህበራዊ ሃላፊነቱን በመወጣት ላይ እንደሚገኝና ይህንን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም