የ26ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ላይ ማሻሻያ ተደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የ26ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ላይ ማሻሻያ ተደረገ

አዲስ አበባ ፤ሚያዝያ 9/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ላይ ማሻሻያ መደረጉን የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ።
የሊጉ ውድድር እየተደረገበት ባለው ሃዋሳ ከተማ ለተከታታይ ሁለት ቀናት ከፍተኛ ዝናብ መጣሉ ተገልጿል።
ሜዳው ከጣለው ዝናብ እንዲያገግም የ26ኛው ሳምንት መርሃ ግብር አንድ ቀን ወደፊት ተገፍቶ ከቅዳሜ ሚያዝያ 11 ቀን እስከ ማክሰኞ ሚያዝያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚደረግ አመልክቷል።
በተጨማሪም በ25ኛው ሳምንት ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ የሚያደርጉት ተስተካካይ መርሃ ግብር ጨዋታ እሁድ ሚያዝያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም በ11 ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚካሄድም ማህበሩ ጠቁሟል።
የድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ ትናንት መካሄድ የነበረበት ቢሆን በከባድ ዝናቡ ምክንያት እንዲራዘም መደረጉ የሚታወስ ነው።