በአለም አቀፍ ደረጃ በቱሪዝም እና ሰላም ተጠቃሿ የሐረር ከተማ

የምስራቋ ፈርጥ ሐረር ባሕላዊ፣ ታሪካዊ ቅርሶችና የቱሪዝም መዳረሻዎች ያቀፈች ከተማ ናት።

ከተማዋ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ከተሞች ብቸኛዋ የአለም ቅርስ ከተሞች ድርጅት(Organization of World Heritage Cities) አባል ከተማ ናት።

በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የተመዘገበ የጁገል የአለም ቅርስ ከተማ።

በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) ሹዋሊድ በዓልን በማይዳሰስ ቅርስነት አስመዝግባለች።


 

በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) በሰላም፤መቻቻልና አብሮነት እውቅና ያገኘች ከተማ።

የአለም ቱሪዝም ከተሞች ፌደሬሽን አባል በመሆን የተመረጠች ከተማ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጣቸው አራት ሙዚየሞች የሚገኙባት ብቸኛ ከተማ።

በአለም ምድብ የብራንዲንግ እና የፓተንት መብት ከተሰጣቸው ሁለት የእደ ጥበብ ውጤቶች አንዱ የሆነው የሀረሪ አለላ ስፌት መገኛ ከተማ።


 

ሀረር ሙቀቷ የማያቅጥል፣ ብርዷ የማይቀዘቅዝ ተስማሚ የአየር ንብረት ያላት በሚል የተገለፀች ከተማ።

እንኳን ሰው፣ጅብን የምታላምድ ውብ ከተማ።

የሐረር ከተማ መቻቻል፣ ፍቅርና አብሮነት የነገሰባት ውበትና ጥበብ የሚቀዳባት ጥንታዊ የስልጣኔ መነሻ መዲና ናት፡፡

ምንጭ፦ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም