ኢትዮጵያ እና ኬንያ የንግድ ስምምነት ተፈራረሙ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ኬንያ የንግድ ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 9/2017 (ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ እና ኬንያ የንግድ ግንኙነታቸውን ማሳለጥ የሚያስችላቸውን የንግድ ስምምነት ተፈራርመዋል።
የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ከትናንት ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የኢትዮ-ኬንያ የድንበር ላይ ንግድ ድርድር መጠናቀቁን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
የድርድሩን መቋጨት ተከትሎ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከኬንያ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ጋር ዛሬ የትግበራ ስምምነት መፈራረማቸውን ጠቁመዋል።
ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት በሚያሳልጥ አግባብ መፈረሙን ጠቅሰው፥ ይህም በድንበር አካባቢ የሚገኙ ህዝቦች መሰረታዊ ፍጆታቸውን ከተሳለጠ አቅርቦት ጋር እንዲያገኙ የሚያስችላቸው ነው ብለዋል።