አርሰናል ሪያል ማድሪድን በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜ አለፈ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 8/2017(ኢዜአ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተጠባቂ ፍልሚያ አርሰናል ሪያል ማድሪድን በደርሶ መልስ ውጤት በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።

ማምሻውን በሳንቲያጎ በርናባው ስታዲየም በተደረገው የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ አርሰናል 2 1 አሸንፏል።

ቡካዮ ሶካ እና ጋብርኤል ማርቲኔሊ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ቪኒሺየስ ጁኒየር ለሪያል ማድሪድ ከሽንፈት ያላዳነችውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።

በጨዋታው ቡካዮ ሳካ ፍጹም ቅጣት ምት ስቷል።


 

ውጤቱን ተከትሎ አርሰናል በድምሩ 5 1 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።

15 ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ሪያል ማድሪድ ጉዞው ሩብ ፍጻሜ ላይ ሲገታ አርሰናል በግማሽ ፍጻሜው ከፒኤስጂ ይጫወታል።


 

በሳን ሲሮ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው የሩብ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ኢንተር ሚላን ከባየር ሙኒክ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።

ላውታሮ ማርቲኔዝ እና ቤንጃሚን ፓቫርድ ለኢንተር ሚላን ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ሀሪ ኬን እና ኤሪክ ዳየር ለባየር ሙኒክ ግቦቹን ከመረብ ላይ ያሳረፉ ተጫዋቾች ናቸው።

ውጤቱን ተከትሎ ኢንተር ሚላን በድምሩ 4 3 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ሲቀላቀል በግማሽ ፍጻሜው ከባርሴሎና ጋር ይጫወታል።

የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች በሚያዚያ ወር መጨረሻ ይደረጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም